Categories: Blog

40/60 & 20/80 condominium lottery successfully held on July 08, 2022. New Information regarding pricing, sites, room types released

[July 9,  2022 Update / ሐምሌ 2 2014 አዲስ መረጃ] – We expect list of names of the winners for 20/80 and 40/60 to be released in the next one or two days. Visit this website later or Download our Android app to get notification when the winner’s list is released / ኮንዶሚንየም ሎተሪ መርሃግብር በተሳካ ሁኔታ አልቋል። የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ሲለቀቅ ፤ በስልኮት ኖቲፊኬሽን እንዲያገኙ ፤ የአንድሮይድ መተግበርያችንን ዳውንሎድ ያድርጉ ወይም ይህንን ገፅ መልሰው ይጎብኙ።

Information regarding 40/60 and 20/80 condominium units that were included in the lottery draw of July 08, 2022 (ሀምሌ 1 ፤ 2014)

Price per square meter for the condominium houses

  • 20/80: 7,997.17 birr per square meter
  • 40/60: 11,162.97 birr per square meter

Sites

  • 20/80: Bereket, Bole Arabsa (sites 3,4 and 5), Wetader, Yeka Tafo, Jemo Gara, Goro Silassie, Fari Hana and Fanuel
  • 40/60: Ayat 2, Bole Beshale and Bulbula Lot 2

People with special privileges that were included in this round were

  • Government employees: 20%
  • Women: 30%
  • For people with disabilities: 5%

Three bedroom 20/80 condominium units were not included in this round due to Administrative decision by the city admin.

Condominium unit types

  • 20/80: 3318 studio houses, 7171 one bedroom houses, 8159 two bedroom houses; a total of 18648 houses.
  • 40/60: 1870 one bedroom, 4220 two bedroom and 753 three bedroom houses in total 6843.

Total number of condominium houses transferred in this round for both 20/80 and 40/60 is 25,491.

You can read the original Amharic news below.

Original Amharic News / ዋናው አማርኛ ዜና

ዛሬ የተላለፉ የጋራ መኖርያ ቤቶችን የተመለከቱ መረጃዎች፡-

👉 አሁናዊ የአንድ ካሬ የቤት ማስተላለፊያ ዋጋ
የሥራ አመራር ቦርዱ ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በወሰነው መሠረት አሁን በሥራ ላይ ያለው አሁናዊ የአንድ ካሬ ማስተላለፊያ ዋጋ፡-
 20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም 7,997.17 ብር
 40/60 ቤት ልማት ፕሮግራም 11,162.97 ብር ነው፡፡

👉 ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የቤት ዓይነትና ብዛት በተመለከተ
 የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም
o አያት 2፤ ቦሌ በሻሌ፤ ቡልቡላ ሎት 2 ሲሆኑ
 የ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም
o በረከት፤ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፤5፤6)፤ ወታደር፤የካ ጣፎ፤ ጀሞ ጋራ፤ ጎሮ ስላሴ፤ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል

👉 በቤት ዓይነትና ብዛት ሲታይ
በ20/80 የቤቱ ብዛት ስቱዲዮ ፡-3318 ባለአንድ መኝታ ፡- 7171 ባለሁለት መኝታ፤- 8159 በድምሩ 18648 ናቸው፡፡
በ40/60 ባለአንድ መኝታ፤- 1870 ባለሁለት መኝታ 4220 እና ባለሶስት መኝታ 753 በአጠቃላይ በድምሩ 25491 ቤቶች ናቸው፡፡

👉 በዚህ ዙር ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የግንባታ አፈጻጸም ሁኔታ በጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በወጣ መመሪያ ቁጥር 3/2011 በሥራ አመራር ቦርድ በማስወሰን
የ20/80 ከ96% በላይ፣ በ40/60 ከ87% በላይ የግንባታ አፈጻጸም ያላቸው ቤቶች ለዕጣ ቀርበዋል፡፡

👉 የዚህ ዙር የዕጣ ተሳታፊዎች ሁኔታ (የቤት ፈላጊ ተመዝጋቢ ሁኔታ) የ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ ለእጣ ውድድር ብቁ የሆኑ እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም ድረስ እና የ40/60 40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም የቆጠቡ ናቸው፡፡

👉 በእጣ ውስጥ የተካተቱት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ከባንክ በተገኘው መረጃ መሠረት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ የዕጣ ተሳታፊዎች ሁኔታ ለዕጣ ከቀረቡ የቤት ዓይነቶች አኳያ በዝርዝር ሲታይ

👉 በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ የሚደረጉ ማህበረሰብ ክፍሎችን በተመለከተ በመመሪያ ቁጥር 3/2011 በተገለጸው መሠረት ከ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) እና 40/60 ተመዝጋቢዎች ውስጥ
 የመንግስት ሠራተኞች 20 በመቶ፣
 ሴቶች 30 በመቶ፣
 አካል ጉዳተኞች 5 በመቶ እና አጠቃላይ ተመዝጋቢዎች 45 በመቶ በዕጣ የቤት ተጠቃሚዎች የሚለዩ ይሆናሉ።

👉 በከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቱን ለመኖር ብቁ ለማድረግ ና ቤቶቹን ለማጠናቀቅ ከባንክ ቦንድ ብድር ብር 18.7 ቢሊዮን እና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ከመደበኛ በጀት ብር 2.871 ቢሊዮን በድምሩ ብር 21.571 ቢሊዮን በሥራ ላይ ውሏል፡፡

👉 በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

👉 በዚህ ዙር ከተላለፉ ቤቶች ውስጥ ከዚህ በፊት በማጣራት ሂደት የተገኙ ቤቶች ለልማት ተነሺ ሲስተናገዱበት ቆይተው የቀሩት ተካተዋል፡፡

👉 የቤት ልማት ፕሮግራም ከጀመረበት አንስቶ በ17 ዓመታት ውስጥ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተቻለው 300 ሺህ ያህል ቤቶችን ብቻ ነው፡፡

👉 የቤት እጣ አወጣጡ እንደ ቅደም ተከተል ሲሆን በ20/80 ፕሮግራም የ97 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ አግኝተዋል፡፡

👉የባለ ሶስት መኝታ ቤት በተመለከተ ፕሮግራሙ ባለፈው ዙር በቦርድ ውሳኔ በመዘጋቱ በቀጣይ በልዩ ሁኔታ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

You can find photos of some of the condominium units below that were transferred in the current round.

View Comments

Share