The 40/60 and 20/80 condominium lottery held on July 8, 2022 has been canceled due to fraud. The city administration has reported that some individuals working mostly on the lottery’s software program have been arrested. The individuals were working for Science and Technology and Housing Development bureau.

10 individuals have been arrested so far ranging from leaders of the bureau to software development officers. Find the original Amharic articles below.

በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ ተደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ዕጣው የተሰረዘውም የከተማ አስተዳደሩ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት መኖሩ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር ድርጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ዝርዝር መረጃ ~ዕጣው ስለተሰረዘው ኮንደምኒየም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫውም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የአጣሪ ቡድን መሪ አቶ በሀይሉ አዱኛ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ነጥቦች ከዚህ እንደሚከተሉት ናቸው፡-
👉 በጋዜጣዊ መግለጫው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመን ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት መፈፀሙን አንስተዋል፡፡
👉 በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ እንዲሁም የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
👉 ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት ጥቆማ ስለደረሰ ጊዜ ሳንሰጥ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል፡፡
👉 የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፡ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል ብለዋል፡፡
 የዚህ ስራ ሌላው አላማ መንግስት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው በማለት ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡
👉 በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን ህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፡፡ ህዝቡን መታደግ ችለናል፡፡
👉 ህብረተሰቡም መብቱን ለማስጠበቅ ያደረግነውን ጥረት ተረድቶናል፡፡ እኛም ድሃውን ማህበረሰብ መታደግ በመቻላችን ያስደስተናል፡፡
👉 የቀረበልን ሪፖርት በሚገባ ሲስተሙ ተቆጣጣሪ ጭምር እንዳለውና አስተማማኝ እንደነበረ ነበር፡፡ ይህንንም ለማመን ምክንያቶች ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በዚህ ቡድን የለሙና ጥቅም ላይ የዋሉ ሲስተሞች ነበሩ፡፡
👉 ማረጋገጫ ለማግኘት የተሄደበትና ተቋም ለተቋም የተደረጉ ግንኙነቶችም ችግር ነበረባቸው፡፡ ሰዎች ለሰዎች የተደረጉ ግንኙነቶች አይነት የተደረጉ ግንኙነቶችም መመልከት ተችሏል፡፡
👉 ኢንሳ ማረጋገጫ ሰጥቶ እንደነበርም በወቅቱ ተገልፆ ነበር ነገር ግን ህጋዊ በሆነ ደብዳቤ ኢንሳ ያረጋገጠው እንዳለሆነ ታይቷል፡፡
👉 ዳታው በሰዎች አጅ ለአምስት ቀን ያህል መቆየቱና ይህም የተከናወነው በሃላፊዎች ትእዛዝ እንደነበር ገልፀዋል
👉 ነገር ግን የምዝገባው ዳታውን በቴሌግራም ጭምር ሲላላኩ እንደነበር በኋላ በምርመራ መታወቁን
👉 በሂደቱም እጣ ቁጠባ ያቋረጡ ሰዎች ፤ቁጠባቸውን ከረሱበት ቦታ ጭምር እጣ እንዲወጣላቸው መደረጉን
👉 የማጣራት ሂደቱን እጣ የወጣ እለት ከሰዓታት በኋላ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡
👉 ይህ የማጣራት ሂደት ኢንሳ አራት ባለሙያዎች መወከሉንና ከዚህ በተጨማሪም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ከብሄራዊ ደህንነት የተዋቀረ ኮሚቴ በኢንሳ አስተባባሪነት ስራውን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
👉 ቴክኖሎጂዎች ለመጠቀም ያደረግነውን ጥረት ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ቴክኖሎጂዎችን የሚያለማው ሰው ቢሆንም ወደፊት በረቀቀ የሙያ ስልት እጣ አወጣጡን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እናድርጋለን
👉 እዚህ በግልፅ ማንሳት የምንፈልገው በወቅቱ የተሰጠን ማብራርያ ከእውነቱ የራቀ መሆኑን በባለሙያዎች ጭምር ተረጋግጧል፡፡
👉 ባለሙያዎችና አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ሃላፊና አንድ ምክትል ሃላፊ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡
👉 ሌሎች እርምጃዎች እንደ ሚዛኑ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
👉 የከተማ አስተዳደሩ አሁንም ቆራጥ አቋሙ ህዝቡን መብት ማስከበረት መሆኑን ይህንን ቤት ለህዝብ ለማቅረብ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ጭምር የጎደለውን መሰረተ ልማት በሟሟላት ለህዝብ ማድረሱን
👉 በፍትሃዊነት ህዝብን ሃብት ለማድረስና የኋላ የኮንዶሚኒየም መጥፎ ታሪክን ላለመድገም ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን፡፡ አሁንም ይቀጥላል፡፡
👉 አሁንም ተቋም ግንባታ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
👉 ስለሆነም በዚህ ሁሉ ችግር እና ሂደት የወጣን እጣ ተዓማኒነት ስለሌለው እጣው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ እንዲሆን አድርገናል፡፡
በአጥፊነት የተጠረጠሩ 10 ኃላፊዎች ታሰሩ
ከ14ኛ ዙር የ20/80 እንዲሁም ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ስም ዝርዝር
1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ
በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-
1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን :_ዳይሬክተር
3ኛ. ሀብታሙ ከበደ :_ሶፍትዌር ባለሙያ
4ኛ. ዬሴፍ ሙላት :_ሶፍትዌር ባለሙያ
5ኛ. ጌታቸው በሪሁን :_ሶፍትዌር ባለሙያ
6ኛ. ቃሲም ከድር :_ሶፍትዌር ባለሙያ
7ኛ. ስጦታው ግዛቸው :_ሶፍትዌሩን ያለማ
8.ኛ. ባየልኝ ረታ ፡_ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ
9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፡_የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ
10ኛ .ኩምሳ ቶላ ፡_ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር
በቀጣይም ሂደቱን እየተከታተልን ለህዝባችን ማድረሳችንን የምንቀጥል ይሆናል፡፡(