Blog

40/60 and 20/80 Condominium Lottery Ceremony to be held on July 08, 2022

[Update / አዲስ መረጃ]
Condominium lottery has successfully been concluded. We expect list of names of the winners for 20/80 and 40/60 to be released soon. Visit this website later or Download our Android app to get notification when the winner’s list is released / ኮንዶሚንየም ሎተሪ መርሃግብር በተሳካ ሁኔታ አልቋል። የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ሲለቀቅ ፤ በስልኮት ኖቲፊኬሽን እንዲያገኙ ፤ የአንድሮይሽ መተግበርያችንን ዳውንሎድ ያድርጉ ወይም ይህንን ገፅ መልሰው ይጎብኙ።

[Update / አዲስ መረጃ] – New details regarding bedroom types, price per square meter, sites and photos have been released. You can find them using the next link -> 40/60 & 20/80 condominium lottery successfully held on July 08, 2022. New Information regarding pricing, sites, room types released.

Addis Ababa City Administration will hold a lottery ceremony to transfer 25,491 condominium house units to registrants under the 40/60 and 20/80 saving scheme. According to the mayor, the administration will transfer houses built under the 40/60 saving scheme for 3rd time while houses built under the 20/80 scheme will be transferred for the 14th time.

The city administration reported that out of the 139,000 houses it had, it has already transferred 96,000 some via lottery, some via administrative decision and the remaining by selecting people using their own criteria.
Out of the 96,000 houses 54,000 house’s keys have already been given to home owners.

Regarding registrants that will be included in this lottery draw, 20/80 registrants who registered on 1997 and have been saving money till February 28, 2022 (የካቲት 21, 2014)  will be included while 40/60 registrants who have saved 40% or more till the same date will be included in the lottery draw.

Total number of people that will be included in the lottery draw will be 27,195 for the 20/80 program and 52,599 for the 40/60 program. As has been the case for the past lottery draws, ‘Displaced Farmers’ will also be included in the current lottery draw.

Ever since the condominium program started 17 years ago, only 300,000 have been built and transferred to home owners.

You can read the full Amharic News Below

Original Amharic News / ዋናው አማርኛ ዜና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው እለት 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ ሊያስተላለፍ ነው ፡፡
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከ2006/07 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታቸው ሲካሄዱ የቆዩ በ40/60 ለ3ኛ ጊዜ እና በ20/80 14ኛ ጊዜ በድምሩ 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡
በመግለጫው ላይ ከተማ አስተዳደሩ የተረከባቸውን 139 ሺህ ስምንት ቤቶች ውስጥ 96ሺህ ያህል ቤቶች በእጣ ፤በውሳኔ እና በምደባ የተሰጡ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ እጣ 25ሺ 491 ቤቶች እጣ እንደሚወጣባቸው አስታውቀዋል፡፡
በተለያየ መንገድ ከተላለፉትም 96ሺህ ቤቶች ውስጥ 54ሺህ ያህሉ ቁልፍ መረከባቸው የተገለፀ ሲሆን ሌሎችም ቁልፍ ያልወሰዱ ቁልፋቸውን እንዲረከቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በ14ኛው ዙር እጣ ብቁ የሚሆኑትን ተመዝጋቢዎች በተመለከተ የ20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም ድረስ የቆጠቡና እና የ40/60 40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው እስከ የካቲት 21 2014 ዓ.ም እንደሚሆኑ ተገልጧል፡፡
በዚህም መሰረት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በዚህ ዙር ዕጣ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡
በዚህ ዙር ከሚተላለፉ ቤቶች ውስጥ ከዚህ በፊት በማጣራት ሂደት የተገኙ ቤቶች ለልማት ተነሺ ሲስተናገዱበት ቆይተው የቀሩት እንዲካተቱ መደረጉን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ባለፉት የቤት ልማት ፕሮግራም ከጀመረበት አንስቶ በ17 ዓመታት ውስጥ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተቻለው 300 ሺህ ያህል ቤቶችን ብቻ መሆኑን ገልፀው ፤አሁንም በሚወጡት ውስን ቁጥር ያላቸው ቤቶች የህብረተሰቡን ችግር መቅረፍ ስለማይችሉ ፤ከተማ አስተዳደሩ አምስት አይነት የቤት ልማት አማራጮችን መዘርጋቱን አስታውቀዋል፡፡
ከነዚህም መሃከል
በመኖርያ ህብረት ስራ ማህበር ፤12ሺህ ያህል ሰዎች ከነበሩት ተመዝጋቢዎች ውስጥ አሁን ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
በመንግስትና በግል ባለሀብቶች አጋርነት /public private partnership/ በ70/30 የግንኙነት ስርዓት
በመኖርያ ቤት በሽርክና ማቅረብ/Joint Venture /፣
የግል አልሚዎች በማበረታታት የህብረተሰቡን የቤት ችግር ለመፍታት አስተዳደሩ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቁጠባ ቤቶችን መገንባት በተመጣጣኝ ኪራይ ማቅረብም አማራጭ
እንደ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አገላለፅ ‹‹ይህ አመራር የተረከባቸው ቤቶች በአጠቃላይ በርካታ ተግዳሮቶች የነበሩባቸው ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ፤የማስተላለፍያ፤ የመሠረተ ልማት አቅርቦት ችግር ፤ የቤቶቹን ግንባታ ጥለው የጠፉ ኮንትራክተሮች ፤ የብድር አቅርቦት እግር እንዲሁም የዋጋ ንረት የመሳሰሉት ተግዳሮቶችን መጋፈጡን አስታውሰዋል፡፡
ነገር ግን እነዚህ እክሎች በማለፍ በአጠቃላይ አስተዳደሩ ከባንክ ቦንድ ብድር ብር 18.7 ቢሊዮን እና ለመሠረተ ልማት ግንባታ ከመደበኛ በጀት ብር 2.871 ቢሊዮን በድምሩ ብር 21.571 ቢሊዮን መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የአንድ ካሬ ማስተላለፊያ ዋጋን በተመለከተም 20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም 7,997.17 ብር 40/60 ቤት ልማት ፕሮግራም 11,162.97 ብር ሲሆን በግል አልሚዎች ከሚሰሩ ተመሳሳይ ቤቶች አኳያ ይህ የአንድ ካሬ ማስተላፊያ ዋጋ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ቀርቧል፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘር ያስሚን ዋህብረቢ በበኩላቸው ቤቶቹ 97 በመቶ አማካኝ አፈፃፀም ላይ የደረሱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አሁን የምንጠቀምበት የእጣ አወጣጥ ሶፍትዌር በተመለከተ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ) ያበለፀገውና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የፌደራልንም ጨምሮ ታይቶ ይሁንታን ያገኘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመበልጸግ ሂደት ብዙ ሙከራዎች የተካደለት ቅድመ-ዝግጅት ለአራት ዙር ሙከራ ተደርጎበት፣ አምስተኛውና የመጨረሻ ዙር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከታዛቢዎች ተገኝቶ እንደሚሞከር ተገልፅዋል፡፡
ሲስተሙ ተጠያቂነትን ማስፈን የሚችል ኦዲት መደረግ የሚችል መሆኑ ገልፀዋል፡፡
• አቶ ሽመልስ ታምራት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የቤት አወጣጡ እንደ ቅደም ተከተል ቅድሚያ የ97 ተመዝጋቢዎች እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የቤት ዓይነትና ብዛት በተመለከተ
የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም
አያት 2፤ ቦሌ በሻሌ፤ ቡልቡላ ሎት 2 ሲሆኑ
የ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም
በረከት፤ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፤5፤6)፤ ወታደር፤የካ ጣፎ፤ ጀሞ ጋራ፤ ጎሮ ስላሴ፤ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል ናቸው፡፡
በዚህ አጋጣሚ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተጀመሩት የተገጣጣሚ ቤቶች የነበረባቸው የፍርድ ቤት እግድ ተነስቶ በፍጥነት እየተገነባ መሆኑ ተገልጧል፡፡

View Comments

Share