ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር
Business Type | NGO |
Mobile 1: | +251924681561 |
Mobile 2: | +251976060511 |
Address: | Bekele Dilla Hotel |
Location: | Dila, Ethiopia |
Number of Employees: | 26-50 |
General Manager: | Mastewal Getnet |
Establishment Year: | 2019 |
If you find a problem with this listing, please let us know by clicking this report link. እዚህ ድርጅት ገፅ ላይ ትክክል ያልሆነ ወይም መስተካከል ያለበት መረጃ ካገኙ ፤ ይህንን ማስፈንጠርያ ተጠቅመው ያሳውቁን።
ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር is listed in the following category
ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር ዲላ በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎች ማህበራዊ ድጋፍ የሚሹ በሚልዮን የሚቆጠሩ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉ ይታወቃል። ምንም እንኳን አባይን በማንኪያ መጨለፍ ቢመስልም ይህንን ማህበራዊ ችግር ሁላችንም የተቻለንን በማድረግ መቅረፍ ይቻላል ብለን በዲላና አካባቢዋ ባሉ ቅን እና የመልካም ልብ ባለቤት ወጣቶች ይህንን ማህበር በ2012 ዓም የመሰረትን ሲሆን ዘር፣ ብሄር፣ ሀይማኖት እና ቦታ ሳይገድበው በኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያውያንን የሚረዳ ነው ከማህበራችን ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካከል:- በዲላ እና በአካባቢው የሚገኙ ጧሪ የሌላቸውን አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች ፣ በከፊል በጎዳና ያሉ ወገኖችን፣ ታራሚዎችን፣ በሆስፒታል እና ቤታቸው ተኝተው የሚታከሙ እና ሌሎች የማህበሩን እገዛ ለሚፈልጉ ሁሉ ፟- ቤት ማደስ፣ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ፣ ማስታመም፣ ንፅህና መጠበቂያዎችን ማደል፣ ማጠብ - የወር አስቤዛ መስጠት፣ በየቀኑ ምግብ ማደል፣የቤት ክራይ መክፈል፣ በዓላትን ከአረጋውያን እና ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ማሳለፍ፣ - በተለያየ ምክንያት ወደጎዳና የወጡ ልጆችን ወደቤተሰባቸው እንዲመለሱ እና ባሉበት እገዛ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የአልባሳት እና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረግ እና -ሌሎች ያልተጠቀሱ እገዛዎችን ማድረግ አላማችሁ አላማችን ነው ብላችሁ ከጎናችን እንደምትሆን ተስፋ እናደርጋለን በጉልበት በሀሳብ ገንዘብ እንዲሁም በቁሳቁስ ማገዝ ለምትሹ:- 0461312600 የቢሮ 0924681561 ህሊና 0976060511 ማስተዋል 0936450843 ነብዩ እንዲሁም በንግድ ባንክ አካውንታችን 1000342158707 ( ኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበር) የቻላችሁትን ማስገባት ትችላላችሁ “ መኖራችን የሚሰማን ለሌሎች ስንኖር ነው ”