You can read the original post in Amharic by clicking the button below this post labeled ‘Original Amharic Post’

<iframe width="1020" height="530" src="https://www.youtube.com/embed/f9UtsuiXs1M" title="YouTube video player" frameborder="0" allow="accelerometer; autoplay; clipboard-write; encrypted-media; gyroscope; picture-in-picture" allowfullscreen></iframe>

It is known that the 12th grade national exam for 2013 E.C was postponed to 2014 E.C due to the country’s situation. A total of 544,568 students (293,856 male and 250,703 female)  have take the postponed exam on Tikimt 29, 2014 E.C. 54,435 (27,979 male and 26,456 female) remaining students who were unable to  take the exam on the postponed  date due to security concerns took the exam on Tir 24, 2014 E.C.

In total, out of the registered 617,991 students 599,003 (321,844 male and 277,159 female students) were able to take which shows a 96.9% coverage.

One the first round civic exam, there have been similarities in the student’s answers which has raised concerns of plagiarism among students. Accordingly, civics will not be considered when calculating final exam rankings.

Students who score 50% or more will be eligible for higher education. Detailed passing marks will be released soon after careful consideration of the Ethiopia’s Universities capacity.

In the mean time, students can find their results using the following methods

  1. result.neaea.gov.et
  2. result.ethernet.edu.et
  3. Telegram Bot:- @moestudentbot
  4. 9444 SMS

Source ምንጭ

Original Amharic Post

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል። የመጀመሪያው ዙር ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293,865 ሴት 250,703 ድምር 544,568 ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27,979 ሴት 26,456 ድምር 54,435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ፈተናው ተሰጥቷል። በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321,844 ሴት 277,159 ድምር 599,003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።

የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ ተከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣ በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል።

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል። ነገር ግን በተናጠል የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 141 ተማሪዎች ላይ ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው የተለያየ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ። ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

  1. በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
  2. በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
  3. በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot – በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የመላኪያ/send/ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።
  4. በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በመጨረሻም ፈተናው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተግባሩን በቁርጠኝነት ለፈጸማችሁ በየደረጃው ላላችሁ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የጸጥታ አካላት ክፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ማሳሰቢያ፡ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሹ አመልካቾች፡- student.ethernet.edu.et በመግባት ማመልከት ይችላሉ። በተመሳሳይ በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎችም result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ። ምላሹንም በማመልከቻ ቅጹ ላይ በሚያስቀምጡት አድርሻ የምናሳውቅ ይሆናል። በአካል ወደ ኤጀንሲው መምጣት አያስፈልግም።

Posted on www.neaea.gov.et