According to Samuel Kifle, head of Ethiopia’s Ministry of Education (MoE), the minimum mark required to attend government universities for natural science students is 363 for male and 351 for female students.
For students in rural areas, the cut off mark has been lowered to 351 for male and 339 for female students. The passing mark for students with hearing disability will be 300 for both male and female students. For students who retook the exam, the cut off mark will be 380. In order to be eligible to join private universities, the cut-off point is 300.

The highest score recorded is 623. For 1st round exam takers the highest mark recorded is 563 while 623 was recorded as the highest score point for 2nd round exam takers. A total of 598,623 students took the grade 12 exam out of which 283,223 scored 50% or above. Out of the 283,223 students, 152,014 are eligible to join government universities while the remaining 135,209 students will seek other higher education alternatives. Out of the 152,014 students joining government universities, 63,883 are female.

Read more in Amharic / ሙሉ ዜናውን በአማርኛ ያንብቡ
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።
በማህበራዊ ሳይንስ አይነስውራን መደበኛ ተፈታኞች ሁለቱም ፆታ 200
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።
በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።በማህበራዊ ሳይንስ አይነስውራን መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 250
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።
ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑ ነው የተነገረው። ከፍተኛ ውጤቱም በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑም ታውቋል።

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600 መያዙ ታውቋል።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152ሺ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙ ተገልጿል።
ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 ፐርሰንት ያህል መሆኑ ተነግሯል።
በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63ሺ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።
የዩኒቨርስቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135ሺ209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ፈተናን በሁለቱም ዙር የወሰዱ 598ሺ 679 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 287ሺ 223 ናቸው ።