Original Amharic News can be found at the end of this article
Amhara Bank will officially start it’s operation on June 18, 2022 (ሰኔ 11 ፤ 2014). The bank has been under formation for quite some time. The bank managed to collect a record breaking 4.8 billion birr in paid up capital and 6.5 billion birr in total capital, making it the most capitalized bank before it even started it’s operations.
On the date of it’s operation commencement, the bank will cover the cost of bus rides via Addis Ababa City Buses in and around Addis Ababa for a full day.
According to Mekaku Fenta, the bank will increase it’s number of branches to more than 100 until Sene 30 (July 07). The bank has also prepared gift packages for mothers who will give birth on the date of operation commencement in selected hospitals located in main cities of regional governments.
Original Amharic News - አማራ ባንክ ሰኔ 11 ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ተገለጸ
በምሥረታ ላይ የቆየው የአማራ ባንክ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ባንኩ አስታውቋል።
በእለቱ ለአዲስ አበባና ዙሪያው ነዋሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ የሙሉ ቀን የጉዞ ክፍያን ባንኩ ይከፍላል ተብሏል።
የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ ባንኩ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ የሚጀምር ሲሆን፤ እስከ ሰኔ ሰላሳ ሥራ የሚጀምሩት ቅርንጫፎች ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚያሳድግም ጠቁመዋል።
ባንኩ በኢትዮጵያ ባለ አክሲዮኖች ብዛት ክብረ ወሰን መስበሩን ያመላከቱት አቶ መላኩ፤ ከፍተኛ የባለ አክሲዮን ቁጥር ማብዛት ብቻም ሳይሆን በውጪም በአገር ውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያን መጠነ ሰፊ ተሳትፎ የተመሠረተ ባንክ ነው ብለዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ባንኩ በተለያዩ የተግባቦት ስርአት የመጣ ሲሆን በዋነኝነትም “ከጎንዎ ማን አለ” የሚለው ማስታወቂያ እንደሚገኝበትም ገልፀዋል።
ሰኔ 11 ሥራውን በይፋ የሚጀምረው ባንኩ በዕለቱ ለአዲስ አበባና ዙሪያው ነዋሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ የሙሉ ቀን የጉዞ ክፍያን ባንኩ ይከፍላል ተብሏል።
በዕለቱ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም የእንኳን ደስ ያላችሁ ስጦታም ይበረከትላቸዋልም ተብሏል።